Search

በደቡብ ጎንደር ዞን ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ገቡ

ሓሙስ ጥር 14, 2018 473

መንግሥት የዘረጋውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ ደቡብ ጎንደር ዞን ባሉ ወረዳዎች በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የታጠቁ ቡድኖች የሰላም አማራጭን ተቀብለው ገብተዋል።

በአቀባበሉ ላይ የተገኙት የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ጥላሁን ደጀኔ፥ አሁንም በጫካ ያሉ ታጣቂዎች የበደሉትን ሕዝብ ለመካስ ሰላምን መርጠው መግባት አለባቸው ብለዋል።

በደቡብ ጎንደር ዞን የሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች ሰላምን ከሚያውኩ አካላት ነጻ እንዲሆኑ የክልል እና የፌዴራል የጸጥታ አካላት ትልቅ ሥራ ሲያከናውኑ እንደነበርም መግለፃቸውን የአማራ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

በቀጣይም የሕዝብ ግንኙነት ሥራዎቻችን በማጠናከር ዘላቂ ሰላምን የመገንባት ሂደቱ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

#EBCDotstream #SouthGondar #Peace