Search

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ከሮተሪ ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

ማክሰኞ ጥር 19, 2018 89

ዶ/ር መቅደስ በዚሁ ወቅት ሮተሪ ኢንተርናሸናል በዓለም ዙሪያ በጤናው ዘርፍ እያከናወናቸው ያሉ ሥራዎችን አድንቀው፤ ይህ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ሮተሪ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ በኢትዮጵያ ደግሞ ከ33 ሚሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስት በማድረግ ፖሊዮ በ99.9 በመቶ ከዓለም እንዲጠፋ ያደረገውን አስተዋጽኦ በአብነት ጠቅሰዋል።

የሮተሪ ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንት ፍራንቸስኮ አሬዞጤና ሚኒስቴር በቅርቡ የማርበርግ ቫይረስ ስርጭትን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠረበትን ትልቅ ስኬት በማንሳት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በሮተሪ ኢንተርናሽናል ፕሬዝዳንት ፍራንሲስኮ ኦሬዞ እና በዲስትሪክ ገዢው ዋሪሙ ንጃጌ የሮተሪ የክብር አባልነት ማዕረግ ተበርክቶላቸው የሮተሪ ኢንተርናሽናል የክብር አባል ሆነዋል።

ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት በአዲስ አበባ የሚገኙት የሮተሪ ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንት ፍራንቸስኮ አሬዞ በቆይታቸው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴን ጨምሮ ከተለያዩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

#EBCDotstream #Ethiopia #MoH #RotaryInternational