የክለቦች የወዳጅነት ጨዋታ አካል በሆነው የስናፕ ድራገን ካፕ ከጣልያኑ ፊዮሬንቲና በኦልድትራፎርድ የተጫወተው ማንችስተር ዩናይትድ መደበኛውን 90 ደቂቃ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል።
ፊዮሬንቲና በሶህም ግብ ጨዋታውን መምራት ችሎ የነበረ ሲሆን፤ ጎሰንስ በራሱ ግብ ላይ ያስቆጠረው ግብ ማንችስተር ዩናይትድን አቻ አድርጓል።
ጨዋታው በዚሁ ውጤት በመጠናቀቁ ወደ መለያ ምት አምርው በዚህም ማንችስተር ዩናይትድ 5 ለ 4 ማሸነፍ ችሏል።
በጨዋታው ላይ የዩናይትድ አዳዲስ ፈራሚዎች ቤንጃሚን ሼሽኮ፣ ብራያን ምቤሞ፣ ማቲያስ ኩንሃ እና ዲዬጎ ሊዮን ከደጋፊው ጋር ተዋውቀዋል።
የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ ኮከብ በረኛ ዴቪድ ዴሂያ በኦልድትራፎርድ ሞቅ ያለ አቀባበል ተደርጎለታል።
በሀብተሚካኤል ክፍሉ
#ebc #ebcdotstream #ebcsport #manchesterunited