Search

በቦረና - ተወዳጁ ቡነ ቀላ

ቦረናዎች የተቆላ ቡና ፍሬን ከትኩስ ወተት እና ቅቤ ጋር አዋህደው የሚያዘጋጁት ቡነ ቀላ የተሰኘ ተወዳጅ መጠጥ አላቸው፡፡
 
ቡነ ቀላ በኦሮሞ ባህል መሰረት ሰዎች የሚመራረቁበት ሲሆን፤ የቦረና የማንነት መገለጫ ከሆኑ ስርዓቶች መካከል አንደኛው
ነው፡፡
 
ሰዎች ሲጣሉ ለማስታረቅ እና እናቶች ሲወልዱ ቡነ ቀላ ተዘጋጅቶ የምርቃት ስነ-ስርዓት ይከወናል፡፡
 
ቡነ ቀላ በገዳ ስርዓት ወቅት፣ በባህላዊ ክንዋኔዎች ወቅት እንዲሁም በማንኛውም ጊዜ ተፈልቶ እንደሚጠጣ የአካባቢው ሽማግሌዎች ያስረዳሉ።
 
ቡነ ቀላ እንግዳም ሲመጣ የሚዘጋጅ ሲሆን፤ ቦረናዎች ቡነ ቀላን ለሚቀርብለት ሰው ያላቸውን አክብሮት የሚገልጹበትም ነው፡፡
 
 
በቦረና ባህል ቡና ትልቅ ክብር እንዳለውም ይነገራል፡፡
 
ረጅም ጉዞ የሚጓዝ ሰው ካለ የተዘጋቸውን ቡነ ቀላ ከመነሻው እስከመድረሻው ጉንጩ ላይ ይዞት እንዲሄድም ይደረጋል፤ ብርታት ይሰጣልና።
 
በቦረና ባህል መሰረት ቡነ ቀላ የቀረበለት ሰው የሚመልሰው ትንሽ አስተርፎ ነው። የቀረውም ቡነ ቀላ ለታታናሾች እና ለሕፃናትም እንደሚሰጥ የአካባቢው አባቶች ይናገራሉ።
 
ይህም መከባበርን እና ስርዓትን ለማስተማር እንደሚረዳ በርካቶች ያስረዳሉ።
 
ኢቢሲ በቅዳሜን አመሻሽ የቦረናዎችን ባህል እና የቡነ ቀላ አዘገጃጀትን አስቃኝቷል።
 
 
በሜሮን ንብረት