Search

ጊዮኬሬሽ የመጀመርያ ግቡን ባስቆጠረበት ጨዋታ አርሰናል አሸነፈ

በኤምሬትስ ዋንጫ አርሰናል አትሌቲክ ቢልባኦን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡
 
በኢምሬትስ በተደረገው ጨዋታ ቪክቶር ጊዮኬሬሽ ቡካዮ ሳካ እና ተቀይሮ የገባው ካይ ሀቨርዝ ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡
 
ከስፖርቲንግ ሊዝበን መድፈኞቹን የተቀላቀለው ቪክቶር ጊዮኬሬሽ ለአርሰናል የመጀመርያ ግቡን አስቆጥሯል፡፡
 
 
 
በጭንቅላት የሚቆጠሩ ግቦች ላይ ብዙም ውጤታማ አይደለም እየተባለ የሚተቸው ኪዮኬሬሽ ዛሬ በተደረገው የአቋም መለኪያ ጨዋታ ላይ በግሩም ሁኔታ በጭንቅላቱ ጎል በማስቆጠሩ አድናቆትን ተቸሮታል።
 
ይህ ጨዋታ ለኪዮኬሬሽ ዓይኑን የገለጠበት ሆኗል ሲሉ በርካቶች ገልጸዋል።
 
የሰሜን ለንደኑ ክለብም የአቋም መለኪያ ጨዋታውን በማሸነፉ የኢምሬትስ ዋንጫን ወስዷል፡፡
 
የመጨረሻ የአቋም መለኪያ ጨዋታውን ያደረገው አርሰናል ቀጣይ ሳምንት በሚጀመረው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመርያ ጨዋታውን ከሜዳው ውጭ ከማንችስተር ዩናይትድ የሚያደርግም ይሆናል፡፡
 
 
በአንተነህ ሲሳይ