የሳዑዲ አረቢያው ክለብ አል ሂላል ዳርዊን ኑኔዝን ከሊቨርፑል ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡
ዩራጓዊው አጥቂ ከሶስት ዓመት የመርሲሳይዱ ክለብ ቆይታ ወደ አል ሂላል ማምራቱም ተረጋግጧል፡፡
አል ሂላል ለተጫዋቹ ዝውውር 46 ሚሊዮን ፓውንድ ወጭ ያደረገ ሲሆን ከክለቡ ጋር ለ3 ዓመት የሚያቆየውን ውል ፈርሟል፡፡
ኑኔዝ ለሊቨርፑል በተሰለፈባቸው 143 ጨዋታዎች 40 ግቦችን ሲያስቆጥር የፕሪሚየር ሊግ እና የካራባዋ ዋንጫንም አሳክቷል፡፡
በአንተነህ ሲሳይ