Search

በጅማ ዞን የተመረተ ከ6.7 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ የአቮካዶ እና የሙዝ ምርት ለገበያ ቀረበ

ቅዳሜ ሐምሌ 18, 2018 50

በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን የፍራፍሬ ምርታማነትን ለማሳደግ በተሰሩ ስራዎች 6.7 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ የአቮካዶ እና የሙዝ ምርት ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ ቀርቧል።

በዘንድሮው የምርት ዘመን በዞኑ 26 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በአቮካዶ፤ እንዲሁም 40 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በሙዝ መልማቱን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት መረጃ ያሳያል።

የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ቲጃኒ ናስር እንዳሉት በዞኑ ባለፉት ዓመታት በተሠሩ ዘርፈ ብዙ የልማት ሥራዎች አበረታች ውጤቶች እየተመዘገቡ ይገኛሉ።

በዚህም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ገበያ ከፍተኛ ተፈላጊነት ያላቸውን ምርቶች በስፋት በማምረት ማቅረብ መቻሉን ገልጸዋል።

በዘርፉ ከሚደረገው የሙያ ድጋፍ ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል በዞኑ የቀርሳ ወረዳ አርሶ አደር የሆኑት አቶ ሀሰን መሀመድ አንዱ ናቸው።

አርሶ አደሮች ለተከታታይ አምስት ዓመታት የአቮካዶ ምርታቸውን ለውጭ ገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተጠቅሷል።

በወሰኑ አውግቸው

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: