Search

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በበጀት ዓመቱ 89 ኩንታል ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቅርቧል - ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን

ቅዳሜ ሐምሌ 18, 2018 270

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን ለክለሉ ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት በበጀት ዓመቱ 89 ኩንታል ወርቅ ተመርቶ ወደ ብሔራዊ ባንክ መላኩን ተናግረዋል፡፡

በግብርናው ዘርፍ በዓመቱ 1.6 ሚሊዮን ሄክታር ማሳ በዘር በመሸፈን ከ55 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡

ለ360 ሺህ 86 ዜጎች የብሔራዊ ድጂታል መታወቂያ የተሰጠ ሲሆን፣ 37 ሺህ 795 ዜጎች የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ሥልጠና መውሰዳቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

ሁለት የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት በሥራ ላይ ሲሆኑ፣ 3 ተጨመማሪ የመሶብ ማዕከላት ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን ርዕሰ መስተዳደር አሻድሊ ሃሰን ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት ገልጸዋል፡፡

የአረንጓዴ ልማት ሥራዎችን በማጠናከር ባለፉት ዓመታ የተተከሉትን ጨምሮ በክልሉ ከ450 ሚሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው ጠቅሰዋል፡፡

በጤና፣ በትምህርት፣ በግብርና፣ በንጹህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በከተማ ልማትና በመሰረተ ልማት ዝርጋታ እንድሁም በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ተሰፋ ሰጪ ሥራዎች መከናወናቸውን ርዕሰ ምተዳደሩ ገልጸዋል፡፡

በጀማል አህመድ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: