Search

ኢትዮ ቴሌኮም እና የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ግብርን በቴሌ ብር ለመሰብሰብ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

ቅዳሜ ሐምሌ 18, 2018 61

ኢትዮ ቴሌኮም አና የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት በባሕርዳር ከተማ ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ፣ የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ግብርን በቴሌ ብር እንዲሰበስብ የሚያስችለው ነው።

ስምምነቱ ዜጎች ያለምንም ድካም እና እንግልት ባሉበት ቦታ ሆነው በቴሌ ብር አማካኝነት ግብራቸውን በቀላሉ እንዲከፍሉ የሚያስችል ስለመሆኑ የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ቢዝነስ ኦፊሰር ብሩክ አዳነ ገልጸዋል።

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፈንታው (/) በበኩላቸው፣ ስምምነቱ የተቋሙን የገቢ አሰባሰብ ሂደት በማዘመን እና ብልሹ አሠራሮችን በማስቀረት ቀልጣፋ እና ፍትሐዊ የገቢ አሰባሰብን የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል።

ቀደም ብሎ ከባሕርዳር ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በክልሉ የተተገበረውን ኤሌክትሮኒክ የታክስ አሥተዳደር ሥርዓት (-ታክስ ሲስተም) በመጠቀም 2018 በጀት ዓመት 90 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉን ቢሮ ኃላፊው ጠቅሰዋል።

ቴሌ ብር ወደ ሥራ ከገባ ጊዜ ጀምሮ በመተግበሪያው 9 ትሪሊዮን ብር የሚጠጋ የገንዘብ ዝውውር ስለመፈፀሙ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል። 60 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን ማፍራትም ተችሏል።

በተስፋሁን ደስታ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: