Search

1447ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል በስኬት ተጠናቋል፦ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ

ዓርብ መጋቢት 11, 2018 40

በታላቅ ድምቀት የተከበረው 1,447ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል፣ በስኬት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።
በዓሉ በስኬት እንዲጠናቀቅ ተቋሙ ከሌሎች የጸጥታና ደኅንነት አካላት ጋር በመቀናጀት፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ሰፊ የሰው ኃይል በማሰማራትና ጥብቅ ክትትል በማድረግ ኃላፊነቱን በአግባቡ ተወጥቷል።
ከበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ በተለያዩ አካባቢዎች በተከናወነው የተጠናከረ ጥበቃ፣ በዓሉ በታለመለት መልኩ በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጉ የጸጥታና ደኅንነት ተቋማት አመራሮችና አባላት ፌደራል ፖሊስ ላቅ ያለ ምስጋናውን አቅርቧል።
በዓሉ በሰላም እንዲከበር ለጸጥታና ደኅንነት አካላት አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ ላበረከቱት ለመላው ሕዝቡ፣ ለሃይማኖት አባቶች፣ ለበዓሉ አስተባባሪዎች፣ ለእምነቱ ተከታዮችና ለወጣቶች ተቋሙ ምስጋናውን ገልጿል።
ይህ የተቀናጀ ጥረት በዓሉ በስኬት እንዲጠናቀቅና የሕዝቡ ደህንነት እንዲጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉም ተመልክቷል።