የኢትዮጵያን ተፈጥሯዊ ውበትና ታሪካዊ ቅርሶች ወደ ላቀ የኢኮኖሚ አቅም ለመቀየር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመረው የገበታ ለትውልድ መርሃ ግብር፣ በአራቱም ማዕዘናት አስደናቂ ውጤቶችን እያስመዘገበ ይገኛል።
ተፈጥሮን ከዘመናዊነት ጋር ያቀናጁት እንደ ደንዲ ኢኮ-ሎጅ፣ ሸበሌ ሪዞርት፣ ገርዓልታ፣ ንኢሌ፣ ሎጎ ሐይቅና ገርባ ዳራ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች፤ ሀገራችንን በአፍሪካ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ የማድረግ ራዕይን እውን እያደረጉ ነው።
እነዚህ መዳረሻዎች ተፈጥሮን ሳይበረዙ ለጎብኚዎች ምቹ ሆነው መገንባታቸው፣ ለሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠሩ ባለፈ የሀገራችንን ገጽታ በአዲስ መልክ እየገነቡት ይገኛል።
ከአፋር ፍልውኃዎች እስከ ቤኒሻንጉል ጥቅጥቅ ያሉ ደኖች፣ ከደቡብ ወሎ መንፈሳዊ መስህቦች እስከ ሶማሊው ዋቢ ሸበሌ ዳርቻ የተዘረጉት እነዚህ ሃብቶች የዛሬ ውበቶቻችን ብቻ ሳይሆኑ ለነገው ትውልድ የምናወርሳቸው የብልጽግና ተስፋዎች ናቸው።
በሃይማኖት ከበደ