ክለቦች በካፍ ክለብ ላይሰንሲንግ ኦንላይን ፕላትፎርም (CLOP) ላይ ሲመዘገቡ ያቀረቧቸውን ሰነዶች መሠረት በማድረግ ያሉበትን ደረጃ አውቀዋል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ኳስ ፌደሬሽን የክለብ ላይሰንሲንግ የፍትህ አካልን መሰረት በማድረግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ያሉበትን ደረጃ ይፋ አድርጓል።
በ2018 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከሚሳተፉት 20 ክለቦች ሁሉንም መስፈርቶች ካለ ማስጠንቀቂያ ማሟላት የቻለው ብቸኛ ክለብ ባህር ዳር ከተማ ሀኗል።
ቀሪ 19 ክለቦች ያላሟሏቸውን ጉዳዮች እንዲያሟሉ የጊዜ ገደብም ተቀምጦላቸዋል።
በውሳኔዎች ላይ ቅሬታ አቅራቢ ክለብ ይግባኝ የመጠየቅ መብቱ የተጠበቀ እንደሆነ ፌደሬሽኑ አሳውቋል።
በአንተነህ ሲሳይ