ኢትዮጵያ ከአንድ ወር በኋላ በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና በይፋ ግብይት እንደምትጀምር የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት ተጠቃሚ እንድትሆን ወደ ውጭ የሚልኩ ነጋዴዎች ዝግጅት እንዲያደርጉ እየተሰራ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ድኤታ እንዳለው መኮንን በተለይ ለኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ገልጸዋል።
ሀገሪቱ በነጻ የንግድ ቀጠናው ከአንድ ወር በኋላ የንግድ ሥራውን ለመጀመር የታሪፍ የቀረጥ ምጣኔ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተወስኖ ሀገራት እንዲያውቁት መደረጉን ሚኒስትር ድኤታው ጠቁመዋል፡፡
በዚህም እስካሁን 22 ሀገራት የየራሳቸውን የታሪፍ ሰነድ ማዘጋጃታቸውን ነው አያይዘው የገለጹት።
የአፍሪካ ነጻ የንግድ ስምምነትን 54 የአፍሪካ ሀገራት የፈረሙ ሲሆን፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ 47 የአፍሪካ ሃገራት ስምምነቱ በሀገራቸው ሕግ ተቀባይነት እንዲኖረው እውቅና ሰጥተው ማጽደቃቸውንም አቶ እንዳለው አንስተዋል።
በየተመኙሽ አያሌው