Search

ግሪሊሽ ወደ ኤቨርተን ለማምራት ስምምነት ላይ ደረሰ

ሰኞ ነሐሴ 05, 2017 375

ኤቨርተን ጃክ ግሪሊሽን ከማንችስተር ሲቲ በውሰት ለማስፈረም ስምምነት ላይ መድረሱ ይፋ ሆኗል።
እንግሊዛዊው ተጫዋች የሕክምና ምርመራውን ዛሬ ያጠናቅቃል ተብሎም ይጠበቃል።
ከማንችስተር ሲቲ ስብስብ ውጭ የሆነው ግሪሊሽ ከመርሲሳይዱ ክለብ ጋር የአንድ ዓመት የውሰት ውል ይፈርማል ተብሎም ይጠበቃል።
በሀብተሚካኤል ክፍሉ