Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን በይፋ መረቁ

ሓሙስ ሚያዝያ 08, 2018 89

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን በይፋ መረቁ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የተገነባውን የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት በይፋ መርቀው ከፍተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ በንፋስ ኃይል አማካኝነት ጨለማን ለመግፈፍ፣ ዐቅምን በለየ የቅድመ ጥናት እና ልዩ ዕቅድ ወደ ተግባር በመግባት ዛሬ የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫን እውን ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።
ይህ ፕሮጀክት 100 ሜጋ ዋት ንጹህ የኃይል አቅርቦት በመጨመር ወደ ዘርፈ ብዙ እና ቀጣይነት ባለው የኃይል መጻዒ ዕጣ ፈንታ ለመገንባት የሚደረገውን ጉዞ እንደሚያጠናክረው አስረድተዋል።
ይህም አስተማማኝ የኃይል አቅርቦትን ለማረጋገጥና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ያለንን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ አብነት መሆኑን ጠቁመዋል።
ለዘመኑ የኃይል ዐቅም ተደማሪ የሆነውን ፕሮጀክት በኩራት እያስመረቁ እንደሚገኙ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ የተገኘው ውጤት መሰል ሥራዎችን ለማበራከት የሚያተጋ መሆኑን ተናግረዋል።
በሁሉም ዘርፎች የሚመዘገበው የኢትዮጵያ የዕድገት ጉዞ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ይበልጥም እየለማ እንደሚሄድ በመጥቀስ፤ "ከምንጊዜውም በላይ ታላቅ የምንሆንበት ጊዜ ሩቅ አይደለም!" ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።