Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የሚገኘውን "ጎበዝ ሶላር ሴል" ማምረቻን ጎበኙ

ቅዳሜ ሚያዝያ 24, 2018 60

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ጠዋት በአዲስ አበባ በሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የሚገኘውን "ጎበዝ ሶላር ሴል" ማምረቻን ጎብኝተዋል።
‎ይህ ፋብሪካ በ2025 ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ያድርጉ ፎረም (Invest in Ethiopia Forum) አማካኝነት በተፈረመው ስምምነት መነሻ በ100 ሚሊዮን ዶላር የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ የተቋቋመ ነው።
‎በውጤታማ ድጋፍ እና ክትትል በስድስት ወራት ብቻ እውን የሆነው "ጎበዝ ሶላር ሴል" ማምረቻ ዘመናዊ ማሽኖች እና በቴክኖሎጂ የተዋቀረ ነው።
‎በመጀመሪያ ምዕራፍ 2 ጊጋዋት ዓመታዊ የማምረት አቅም ያለው ፋብሪካው የኢትዮጵያን የኃይል ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ከታዳሽ ኃይል ለማድረግ የተጀመረውን ሀገራዊ ርዕይ እውን ለማድረግ ተደማሪ አቅም ፈጥሯል።
‎በተጨማሪም በኢንደስትሪ ፓርኩ ውስጥ የሚገኘውን የጫማ ማምረቻ እና ንዑስ የኤሌክትሪክ ጣቢያን መመልከታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት ጠቁመዋል።