ሙኒራ ኢብራሂም ትባላለች። በአፋር ክልል የአዋሽ 7 ከተማ ነዋሪ ናት።
በከተማ የሚከናወኑ የተለያዩ የበጎ ፍቃድ ሥራዎች ላይ ግንባር ቀደም ሆና ትሳተፋለች።
ማህበራዊ ኃላፊነቷን በመወጣቷ ደስተኛ መሆኗን ትናገራለች።
ሙኒራ በከተማዋ ሁለቱም ኩላሊቶቹ ሥራ አቁመው የነበረውን የወጣት ማህዲ ተኮላን ታሪክ ትሰማለች።
ባለፉት ሁለት ዓመታት ለኩላሊት እጥበት ከፍተኛ ወጪኝ ሲያወጣ የነበረው ወጣት ደግሞ የከፋ ችግር ላይ ነበር።
ቤተሰቦቹ ያላቸው ንብረት እየሸጡ ለኩላሉት እጥበት እና ለተለያዩ ሕክምናዎች ሲያውሉ ቆይተዋል።
ይህን ጊዜ ሙኒራ የሚቻላትን ሁሉ ማድረግ እንዳለባት መወሰኗን ትናገራለች።
የእርዳታ ሥራዋን ስትጀምር ልቧ በሀዘን ተሞልቶ እንደነበር አትዘነጋውም።
በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥም ለኩላሊት ተማሚው የሕክምና ወጪ የሚውል ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ በማሰባሰብ በጎ ተግባሯን ማጠናከርም ችላለች።
አሁን ላይ የታማሚው እናት ኩላሊት ተመርምሮ ለልጃቸው ሕክምና ኩላሊታቸውን መሰጠት እንደሚትችሉ በሐኪሞች ስለተነገራቸው ወደ ሕንድ ሀገር ሄደ ንቅለ ተከላ ለማካሄድ ተጨማሪ ድጋፍ እየጠየቁ ይገኛሉ።
ለኩላሊት ንቅለ ተከላው 5.5 ሚሊዮን ብር የሕክምና ወጪ ስለሚያስፈልግ ይህ ገንዘብ ከአቅማቸው በላይ የሆነው የታማሚው ቤተሰቦች እጃቸው ለእርዳታ ዘርግተዋል።
በአፋር ክልል ከተለያዩ አከባቢዎች የሚገኙ ዜጎች የዚህን ወጣት ሕክምና ወጪ በመሸፈን ከፈጣሪ በታች የወጣቱን ሕይወቱን ለማትረፍ ድጋፍ እያቀረቡም ይገኛል።
ሙኒራ ኢብራሂምም "የማህዲ እናት ልጄን አድኑልኝ የሚል ተማጽኗቸውን ዛሬም አስታውሳለሁ እና ወጣቱ ድኖ እስከማየው ድረስ የበጎ ፈቃድ ሥራውን አላቋርጥም" ስትል ተናግራለች።
በሁሴን መሃመድ
#EBC #ebcdotstream #Kidney # volunteris