ማንችስተር ዩናይትድ ከአርሰናል የሚያደርጉት የነገ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታ ተጠባቂ ነው። ይህን ጨዋታ ማን ያሸንፋል?
አንጋፋውጋዜጠኛ ዮናስ አዘዘ በዚህ ዙርያ ሙያዊ ትንታኔውን በነገው የቅዳሜ መልክ የዜና መሰናዶ ያጋራናል።
የነገ ነሀሴ 10 የቅዳሜ መልክ የስፖርት ትንታኔ ሰዓት እንግዳችን አንጋፋው ጋዜጠኛ ዮናስ አዘዘ ነው።

ዮናስ አዘዘ በፋና ኤፍ ኤም 98.1 እና በብሰራት ኤፍ ኤም 101.1 በስፖርት ጋዜጠኝነት ሰርቷል።
በሱፐር ስፖርት ላለፉት 5 ዓመታት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና በውጭ ሊጎች ተንታኝነት አገልግሏል፤ በአራት ሦስት ሦስት የሬዲዮ ፕሮግራምም ተንታኝ ነው።
ሁለገቡጋዜጠኛ በነገው የቅዳሜ መልክ ፕሮግራም የስፖርት ትንታኔ ሰዓት ማንቸስተር ዩናይትድ ከአርሰናል የሚያደርጉትን ጨዋታ ይተነትንልናል።
ነገ ማለዳ ከ2፡00 – 5፡00 የቅዳሜ መልክ የዜና መሰናዶ በኢቲቪ ዜና ቻናል እና በዶትስትሪም የማሕበራዊ ሚዲያ አማራጮች ወደ እናንተ በቀጥታ ይደርሳል። ይጠብቁን!