Search

ሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ በሀዋሳ ከተማ አቀባበል ተደረገለት

ሰኞ ሐምሌ 06, 2018 94

2018 ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ የሆነው ሲዳማ ቡና በሀዋሳ ከተማ ደማቅ አቀባበል እየተደረገለት ነው።

68 ነጥብ በመሰብሰብ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን የሆነው ቡድኑ፤ ከኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ በኋላ ወደ ሀዋሳ ከተማ ሲመለስ የከተማውና አካባቢው ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል እያደረጉለት ይገኛል።

የቡድኑ አባላት በክፍት ተሽከርካሪ ሆነው በከተማው በመዘዋወር ደስታቸውን እየገለፁ ነው።

ቡድኑ ከቀናት በፊት በተካሄደው የኢትዮጵያ ዋንጫ ተሸንፎ ጥምር የዋንጫ አሸናፊ የመሆን ውጥኑ ባይሳካም፤ የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን መሆኑን ተከትሎ በቀጣይ የውድድር ዓመት በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ኢትዮጵያን ይወክላል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: