ማንቸስተር ዩናይትድ ቤልጂየማዊውን አማካይ ዩሪ ቲሌማንስን ከአስቶን ቪላ በ36 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ አስፈርሟል።
የ29 ዓመቱ ተጫዋች በኦልድ ትራፎርድ ለአምስት ዓመታት የሚቆይ የኮንትራት ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን፣ ይህም ዝውውር የክለቡን የአማካይ ክፍል ይበልጥ ያጠናክረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
ቲሌማንስ ዝውውሩን ተከትሎ በሰጠው አስተያየት፣ "እንደ ማንቸስተር ዩናይትድ ያለ ታላቅ እና ልዩ ክለብ መቀላቀሌ የሚሰማኝን ስሜት በቃላት መግለጽ ይከብደኛል፤ ይህ ዝውውር እግር ኳስን መውደድ ከጀመርኩበት ጊዜ አንስቶ ለለፋሁት ልፋት ትልቁ ስኬቴ ነው" ብሏል።
አክሎም፣ የክለቡ አመራሮች እና ተጫዋቾች በቀጣይ ዓመታት ታላላቅ ዋንጫዎችን ለማሸነፍ ያላቸው ጽኑ ፍላጎት እጅግ ግልጽ እንደሆነና እሱም ለዚህ ስኬት የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ መጓጓቱን ተናግሯል።
በዘረንቶስ ሰለሞን
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: