Search

የኢትዮጵያን ችግሮች በጠረጴዛ ዙሪያ የመፍታት ጉዞ

ሰኞ ሐምሌ 06, 2018 53

ውይይት እና ምክክር የኢትዮጵያ ነባር እና ታሪካዊ እሴቶች በመሆናቸው ሀገራችን የገጠሟትን ማኅበራዊና ፖለቲካዊ አለመግባባቶች በሐቀኛ ምክክር ለመፍታት ቁርጠኛ አቋም ይዛ እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች።

መላው ጥቁር ሕዝብ የሚኮራበትን የዓድዋ ድል ያስመዘገበችው፣ የሰው ዘር መገኛ፣ የራሷ የዘመን አቆጣጠርና ፊደል ያላት እንዲሁም ገዳ ሥርዓትን የመሳሰሉ ጥንታዊ የዴሞክራሲ እሴቶች ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ፣ ሉዓላዊነቷን ለማስከበርና ድህነትን ለማሸነፍ በምታደርገው ሁለንተናዊ ጥረት ውስጥ የውስጥ ችግሮቿንም በጠረጴዛ ዙሪያ የመፍታት ተግባራዊ እርምጃዎችን በግንባር ቀደምትነት እያከናወነች ነው።

በኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ዘንድ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት፣ ማኅበራዊ ትሥሥርን ለማጠናከርና የሀገርን አንድነት ለመጠበቅ በየአካባቢ ያሉ ባሕላዊ የሽምግልና ሥርዓቶች ለዘመናዊው የዳኝነት ሥራ አዎንታዊ አስተዋጽዖ ሲያበረክት ቆይቷል።

ይሁን እንጂ ለዘመናት ትኩረት ሳይሰጣቸው የቆዩና በጊዜ ሂደት እየተካረሩ የመጡ ፖለቲካዊ ልዩነቶች የውይይት ባሕሉን በመሸርሸር ሀገራችንን ለግጭትና ለጦርነት ለመዳረግ ቢያስቡም እነዚህን መሠረታዊ ተቃርኖዎች በዘላቂነት ለመፍታት ከባሕላዊ ሥርዓቶች የተቀዳ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ተቋቁሞ በትኩረት እየሰራ ይገኛል።

ኮሚሽኑ ከሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሃይማኖት አባቶች እና ከሲቪክ ማኅበራት የተውጣጡ አካላትን ያሳተፈ የአጀንዳ ማሰባሰብና የተሳታፊ ልየታ ሥራዎችን ሙሉ በሙሉ አከናውኗል።

በዚሁም ኮሚሽኑ የሐሳብና የውክልና አካታችነትን ባረጋገጠ መልኩ ዜጎች አጀንዳዎቻቸውን በነፃነት እንዲያቀርቡና እንዲደማመጡ አድርጓል።

ኢትዮጵያ ያሉባትን ፈተናዎች እና የቆዩ ፖለቲካዊ አለመግባባቶችን ፍጹም ግልጽ፣ ገለልተኛና አሳታፊ በሆነ መንገድ ለመፍታት አጀንዳዎችን ለይታ ትልቁ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ለሐምሌ 8 ቀን 2018 . እየተጠበቀ ይገኛል።

በብሌን ደምበሎ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: