ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀድሞው የኳታር አሚር ሼክ ሐማድ ቢን ኸሊፋ አል ታኒ ኅልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ለመግለጽ ኳታር ገብተዋል።
ይህ ጉብኝታቸው በኢትዮጵያ እና በኳታር መካከል ያለውን የረጅም ዘመን ወዳጅነት የሚያሳይ ከመሆኑም ባሻገር፣ በቀጣናው እና በዓለም ላይ ዘላቂ አሻራ ጥለው ያለፉትን የመሪውን ትሩፋት የሚያከብር መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ገልጿል።
የቀድሞው የኳታር አሚር ሼክ ሐማድ ቢን ኻሊፋ አል ታኒ ነፍስ በሰላም ትረፍ ሲል የተመኘው ጽ/ቤቱ፣ በዚህ የኀዘን ወቅትም ለኳታር ሕዝብ መጽናናትን እና ብርታትን ተመኝቷል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: