የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ጌዛ አንድሪያስ ፎን ጋየርን (ዶ/ር) በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሚኒስትር ዴኤታው ጋር በነበራቸው ውይይት ጀርመን የኢትዮጵያ ቁልፍ የልማት ትብብር እና የንግድ አጋር መሆኗን ገልጸዋል።
በዓለም አቀፍ አጀንዳዎች ዙሪያም ያላቸው ተባብሮ የመሥራት ልምድ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አንስተዋል።
ጌዛ አንድሪያስ ፎን ጋየር (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ሀገራቸው የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ምርቶች መዳረሻ እንደመሆኗ የኢኮኖሚ ግንኙነቱ የበለጠ ለማጠናከር መሥራት እንደሚገባ አመልክተዋል።
ሁለቱ ወገኖች በሰለጠነ የሰው ኃይል ሥምሪት፣ በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል እና መቋቋም ዙሪያ የመከሩ ሲሆን፣ በወቅታዊ ቀጣናዊ እና መካከለኛው ምሥራቅ ጉዳዮች ዙሪያም ሐሳብ መለዋወጣቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: