ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሐመድ (ዶ/ር) በሀገራዊ ምክክር ጉባዔ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው ካደረጉት ንግግግር ውስጥ ቁልፍ መልዕክቶቹ፦
ታሪካዊ ዕድል፦ ይህ ጉባኤ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ በስፋቱና በዓላማው እጅግ የገዘፈ ነው። ይህንን የታሪክ አጋጣሚ ለትውልድ የሚበጅ በጎ ታሪክ ለመጻፍ መጠቀም ይገባል።
መከራን ወደ ዕድል መቀየር፦ በኢትዮጵያ ያለፉትን ችግሮችና መከራዎች ወደ ዘላቂ መፍትሄ በመቀየር ለልጆቻችን የተሻለች አገር ማስረከብ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው።
የፖለቲካ ባህል ስብራት፦ የኢትዮጵያ ፖለቲካ በኃይለ ቃል ጀምሮ በኃይል እርምጃ የመደምደም ባህል አለው። ይህንን ስብራት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በአገር አቀፍ ምክክር ማቆም ያስፈልጋል።
የጣልቃ ገብነት ሥጋት፦ አገሪቱ በውስጥ አለመግባባት ውስጥ በገባች ቁጥር፣ በልማት ላይ የማይታዩ ነገር ግን ግጭት ሲኖር የሚያንዣብቡ የውጭ ኃይሎች (አሞሮች) አሉ። የኢትዮጵያ ጥቅምን በውስጥ መወያየትና መፍታት እነዚህን ኃይሎች ያከሽፋል።
የመደማመጥ አስፈላጊነት፦ እውነተኛ መፍትሄ የሚመጣው ትልልቅና ትናንሽ ብሔሮችን እኩል በማክበርና በመደማመጥ ነው። ለኢትዮጵያ እንጂ ለግል ወይም ለሰፈር ጥቅም ብቻ መመካከር አይጠቅምም።
የጋራ መግባባት ዘመን፦ አራት ሺህ ሰዎች ተሰብስበው የሚመክሩት ለዛሬ ብቻ ሳይሆን፣ ወደፊት ለሚመጡ ትውልዶች የሚሻገር የጋራ መግባባትና ሕገ-መንግሥታዊ መሠረት ለመጣል ነው።
ቀፎ ውስጥ መቆየት፦ "ቀፎዋን የጣለች ንብ ማር አትሰጥም"። ተወካዮች ማር (ውጤት) ለመስጠት ሀሳባቸውና ልባቸው እዚሁ ጉባኤ አዳራሽ ውስጥ መሆን አለበት፤ ከውጭ በሚመጡ ፕሮፖጋንዳዎች መዘናጋት የለባቸውም።
የማስፈጸም ኃላፊነት፦ ኮሚሽነሮችና ተሳታፊዎች በጀግንነት የተረከቡትን ኃላፊነት በመወጣት፣ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ምሳሌ የምትሆን ሰላማዊ አገር ለማድረግ መትጋት አለባቸው።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: