Search

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት የ6ኛ ዘመን 11ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

ሰኞ ሐምሌ 20, 2018 177

በጉባኤው ላይ የ6ኛ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤን በማፅደቅ የጀመረ ሲሆን ምክር ቤቱ በቆይታው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ እንደሚመክር የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አያን አብዲ ተናግረዋል።

የሶማሌ ክልላዊ መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርትን ማዳመጥ እና ማፅደቅ፣ የክልሉ ምክር ቤት ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርትን ማዳመጥ እና ማፅደቅ፣ የፍርድ ቤት እና ዋና ኦዲተር ሪፖርቶችን ማዳመጥ እና ማፅደቅ ከተቀመጡ አጀንዳዎች መካከል ተጠቃሾቹ ናቸው።

ምክር ቤቱ በመጨረሻም የክልሉን የ2019 በጀት ዓመት ዓመታዊ በጀትን እንዲሁም የተለያዩ ሹመቶችን በማፅደቅ ጉባኤውን እንደሚያጠናቅቅ የወጣው መርሐ ግብር ያሳያል።

በቴዎድሮስ ታደሰ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: