Search

ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምን በማስፈን የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ነው

ሰኞ ሐምሌ 20, 2018 38

ኢትዮጵያ በቀጣናው ሽብርተኝነትን በመዋጋት እና ሰላምን በማስፈን ግንባር ቀደም ሚናዋን እየተወጣች መሆኑን የመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን እስማኤል ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ከአሜሪካ አፍሪካ ዕዝ (AFRICOM) ጋር በመተባበር የምታስተናግደው የአፍሪካ ሎጂስቲክስ እና ኮሙኒኬሽን ሲምፖዚዬም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በመርሐ ግብሩ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሐመድ፣ የአሜሪካ የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰን፣ የመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን እስማኤል፣ የሀገራቱ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች እና የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የጦር መሪዎች ታድመዋል።

የመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን እስማኤል በዚሁ ወቅት እንዳሉት ኢትዮጵያ ለቀጣናው ብሎም ለዓለም ሰላም እና ደኅንነት ያላት ቁርጠኝነት ዘመናትን የተሻገረ ነው፡፡

በዚህም ኢትዮጵያ በቀጣናው ሽብርተኝነትን በመዋጋት እና ሰላምን በማስፈን ግንባር ቀደም ሚናዋን እየተወጣች መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የተሟላ የሎጅስቲክ እና ኮሙኒኬሽን ሥርዓት በማረጋገጥ ሽብርተኝነትን በመከላከልና ሰላምን በማስፈን የተሳካ ተልዕኮ ፈጽማለች ብለዋል፡፡

የተደራጀ የኮሙኒኬሽን ሥርዓት ካልተደራጀ አስቸጋሪ ነው ያሉት ኃላፊው፤ ለዘርፉ የሚሰጠውን ትኩረት ከዘመኑ ጋር በዋጀ መንገድ ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

መድረኩ በዘመቻና ስምሪት ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት ዘመናዊ ስልት መቀየስ የሚያስችል ዕድል መፍጠር ያስችላል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: