በ2018/19 የምርት ዘመን በመኸር ወቅት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ 2 ሚሊዮን 48 ሺሕ ሔክታር በላይ ማሳ በዘር በመሸፈን ከ73 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል።
የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ሃጂ ባበክር ኸሊፋ እንዳገለጹት በክልሉ በየዓመቱ የሜካናይዝድ እርሻዎች እየተስፋፉ መምጣታቸውን እና አርሶ አደሮች የክላስተር ማሣን ውጤታማነት በመረዳት በንቃት እያለሙ ይገኛሉ ብለዋል ።
የግብዓት አቅርቦትም ጊዜውን ጠብቆ እንዲሰራጭ መደረጉን ጠቅሰው እስከ አሁን በክልሉ ከ1.5 ሚሊዮን ሔክታር በላይ ማሣ በተለያዩ ሰብሎች መሸፈኑን አንስተዋል።
በአሶሳ ዞን የባምባሲ ወረዳ ነባር ቀሽማንዶ ቀበሌ አርሶ አደሮች በበኩላቸው በአንድ አካባቢ ከ250 ሔክታር በላይ ማሣን በበቆሎ ክላስተር ማልማታቸውን ገልጸዋል።
አርሶ አደሮቹ በክላስተር እርሻ በመሰማራታቸው ምርታማነታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱንም ተናግረዋል ።
ምርታማነትን ማሳደግ እና የአርሶ አደሩን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ለሀገር አቀፍ የኢኮኖሚ ዕድገት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተመላክቷል።
በነስረዲን ሀሚድ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: