መንግሥት ካስቀመጣቸው አምስት ቁልፍ የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ምሰሶዎች መካከል አንዱ የሆነውን የቱሪዝም ዘርፍ ለማሳደግ፣ በታሪካዊቷ የሐረር ከተማ ሰፊ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።
ጥንታዊ ውበቷን ከዘመናዊ ገጽታ ጋር በማሰናሰል አዲስ ገጽታን የተላበሰችው ሐረር፣ አሁን ላይ እየተተገበረ ባለው የኮሪደር ልማት እና የቅርሶች ዕድሳት ሥራ የቱሪዝም ዘርፉን ይበልጥ አነቃቅታለች።
የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ሀብት የሆኑት የሐረር ጀጎል ጥንታዊ፣ ሃይማኖታዊ እና ታሪካዊ ቅርሶች ይዘታቸውን ጠብቀው እንዲለሙ እና ለትውልድ እንዲተላለፉ የመደመር ዕሳቤ ያመጣው ሕያው ትሩፋት ነው።
ይህ በዘርፉ የተሰጠው ልዩ ትኩረት ለአደጋ ተጋልጠው የነበሩ ቅርሶችን ከማዳኑም ባሻገር፣ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማስፋት እና የጎብኚዎችን ቆይታ በማራዘም ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ አቅም በእጅጉ አሳድጎታል።
በክልሉ የተከናወኑት ስኬታማ የቱሪዝም ማጎልበት ተግባራት፣ ከውጭ ሀገር ቱሪስቶች በተጨማሪ የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች እና የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ሐረርን በስፋት እንዲጎበኙ እና አስደናቂ ውበቷን ለዓለም እንዲያስተዋውቁ ሰፊ ዕድል ፈጥሯል።
የመደመር ትውልድ የትናንትን ታሪክ ከዛሬ ጋር በማስተሣሠር፣ ከትናንት ወረቶቻችን መልካሙን ወስዶ በማላቅ፣ የዛሬውን ጥረት አክሎበት ለነገው ትውልድ የሚያኮራ ቅርስ እያስተላለፈ ይገኛል።
ትናንት የነበሩንን ጠንካራ ነገሮች ሳናፈርስ፣ ያለፈውን ስብራት ጠግነን በማብቃት የሠራነው ታሪክ በእውነትም ትውልድ የማይዘነጋው አኩሪ ገድል ነው።
በአዲስ መልክ እና ቀለም የተዋበው ጀጎል የሐረርን ቀደምት ሥልጣኔ እየመሰከረ የሀገርንም ገጽታ እየገነባ ይገኛል። - መረጃው የሐረሪ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ነው።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: