በሀገራዊ ምክክር የመክፈቻ ሥነ - ሥርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ኢትዮጵያ በማንኛውም ፈተና ውስጥ ብታልፍም ማዕበሉን ወደ ድል የመቀየር አቅም እንዳላት ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ መሰረት ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ባህልን የምታጸናበት እና ለቀጣይ ትውልድ የሚተርፍ መልካም መሰረት የምትጥልበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መሆኗን አስታውቀዋል።
“የጀመርናቸውን መልካም ዘሮች እንዘራለን፣ እንንከባከባለን፣ ዛፍ እናደርጋቸዋለን፤ ነገር ግን ከሚያፈሩት ፍሬ እኛ ሳንሆን ትውልድ እንዲጠቀም እናደርጋለን” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ጉባኤ ለኢትዮጵያ ብልጽግና እና ሰላም ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው እምነታቸውን ገልጸዋል።
ሀገራዊ ምክክሩ የኢትዮጵያን የጋራ መግባባት በማጠናከር ረገድ የላቀ ፋይዳ እንዳለው የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የተመካካሪዎቹ የጋራ ጥረት ለወደፊት ትውልድ የሚበጅ ዘላቂ ሃሳብ እንደሚያመነጭ ተስፋቸውን ሰንቀዋል።
በጌቱ ላቀው
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: