በዓለም ታሪክ ውስጥ በግጭት የተገነባ ወይም ያተረፈ ሀገር አለመኖሩን አስገንዝበዋል። አክለውም በፖለቲካ ባህል ውስጥ ልዩነቶች መኖራቸው ተፈጥሮአዊ ቢሆንም፤ ትልቁና መሰረታዊው ስህተት ግን እነዚህን ልዩነቶች በኃይል ለመፍታት መሞከር እንደሆነ ነው ያነሱት። ከሁሉ በላይ ልዩነቶችን መፍታት የሚቻለው በሰላማዊ መንገድ፣ በመነጋገርና በተለያዩ ሰላማዊ መድረኮች መሆኑን ያብራሩት ዋና ፀሐፊው፤ ኢትዮጵያም ለዚህ የሚሆኑ በርካታ ባህላዊ የምክክር መንገዶች ያሏት ሀገር መሆኗን ጠቅሰዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: