Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይና የደኅንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ ጋር ተወያዩ

ረቡዕ ሐምሌ 08, 2018 98

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይና የደኅንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ ካያ ካላስን ተቀብለው ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ በአውሮፓ ሕብረት እና በአፍሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር ላይ መምከራቸውን አመልክተዋል።

በጋራ ጥቅሞች እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሐሳብ መለዋወጣቸውንም ጠቁመዋል።

በተጨማሪም ትኩረት የሚሹና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መሠረት ባደረገው ውይይታችን፤ ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ይበልጥ ለማሳደግና ለማስፋፋት በሚያስችሉ መንገዶች ላይ መክረናል ሲሉም ገልጸዋል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: