Search

የአዋሽ ባንክ 8ኛውን ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር አከናወነ

እሑድ ሐምሌ 12, 2018 112

የአዋሽ ባንክ 8ኛውን ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ከእኅት ኩባንያው አዋሽ ኢንሹራንስ ጋር በመተባበር "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በምሥራቅ ሸዋ ዞን በቢሾፍቱ ከተማ አደአ ወረዳ አካሂደዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የተቋማቱ አመራሮች፣ ሠራተኞች እና የማኅበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ተገኝተዋል።

የደን መመናመንን ለማስቀረት እና የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመከላከል የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ፣ ባንኩም ይህንን ዐሻራ ለትውልድ ጥሎ ለማለፍ ያለመ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

ኤጂያ እንጂፈታ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: