የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የማስፈጸም አቅም እየጠነከረ መምጣቱን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገልጸዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በ6ኛው ጨፌ 5ኛ የሥራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ከጨፌው አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የማስፈጸም አቅም እየጠነከረ መምጣቱን አንስተው፣ ይህ ጥንካሬ ለሕዝቡ ተስፋ መሆኑን ተናግረዋል።
"ሕዝባችን ከአመራሩ ጋር በጋራ በመሆን ሀገርን እያሻገረ ነው" ያሉት አቶ ሽመልስ፣ "የሕዝባችንን አቅም በጥልቀት መረዳት ያልቻሉ ወገኖች ዛሬ ላይ የሐሰት ሕልም እያለሙ ይገኛሉ" ብለዋል።
በገጠር አካባቢዎች እየተገነቡ ያሉ የ"ሀሮሜ" መንደሮች ቤቶች ምቹ ከመሆናቸው ባለፈ የራሱ የገበሬው ሀብት እና ንብረት እየሆኑ መምጣታቸውንም በማብራሪያቸው አንስተዋል።
ይህም በአንድ በኩል የሕዝቡን ኑሮ እያሻሻለ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ኢንቨስትመንትን እና የገጠር ከተማነትን እያስፋፋ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የ"ሀሮሜ" ፕሮግራም የገጠሩን ማኅበረሰብ ወደ ዘመናዊነት በማቅረብ በልማት እንቅስቃሴ ውስጥ እንዲሳተፍፉ የሚያደርግ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሽመልስ፣ ሁሉም የ"ሀሮሜ" ቤቶች የባለቤትነት መብታቸው ሙሉ በሙሉ ለአርሶ አደሩ የሚሰጥ መሆኑን አብራርተዋል።
በሃይማኖት ከበደ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: