Search

“መነሻዬም ታሪኬም ከዚህ ነው”፦ የካናዳው ኮከብ እና ትውልደ ኢትዮጵያውያው አሊ አህመድ ወደ እናት ሀገሩ መጣ

ሰኞ ሐምሌ 13, 2018 136

2026 የዓለም ዋንጫ ከካናዳ ብሔራዊ ቡድን ጋር ታሪካዊ ጉዞ ማድረግ የቻለው ተሰጥኦ ያለው የኖርዊች ሲቲ እና የካናዳ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አሊ አህመድ፣ ለሶስት ቀናት በሚቆይ ይፋዊ የጉዞ መርሐ-ግብር ወደ እናት ሀገሩ ኢትዮጵያ መጥቷል።

አሊ ከኢትዮጵያ ጋር ስላለው ጥልቅ ቁርኝት በደስታ ስሜት ሲናገርመነሻዬም ሆነ ታሪኬ የሚጀምረው ከዚህ ነውበማለት ወደ ሀገሩ በመመለሱ የተሰማውን ታላቅ ኩራት ገልጿል።

በቆይታው የተለያዩ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ የቱሪስት መስህቦችን እንደሚጎበኝ የተገለጸ ሲሆን፣ ወደፊትም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ መድረክ ላይ በደማቁ ተሳትፎ እንደሚያደርግ አዎንታዊ ምኞቱን አጋርቷል።

የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ መኪዩ መሐመድ ተጫዋቹን አቀባበል ያደረጉለት ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስኬታማ የሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መምጣት ለቀጣዩ የኢትዮጵያ ወጣቶች ትልቅ ተስፋና አርአያ እንደሚሆን አስረድተዋል።

በመርሐ-ግብሩም ላይ አቶ መኪዩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መለያን ለተጫዋቹ በስጦታ አበርክተውለታል። ስፖርት ለሀገር ገጽታ ግንባታ እና ለወጣቶች መነሳሳት ያለው ሚና እጅግ ከፍተኛ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን፣ ይህ ጉብኝትም የትውልደ ኢትዮጵያውያንን ከሀገራቸው ጋር ያለውን ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር ታሪካዊ ክስተት ሆኗል።

በአሜሪካው ሜጀር ሊግ ሶከር ባሳየው አስደናቂ ብቃት ምክንያት በጥር 2026 ወደ እንግሊዝ አምርቶ ለኖርዊች ሲቲ የፈረመ ሲሆን፣ በመጀመሪያ ዓመቱ ግቦችን በማስቆጠርና ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል ፈጣን ተፅዕኖ መፍጠር ችሏል።

አሊ አህመድ ለካናዳ ብሔራዊ ቡድን 28 ጨዋታዎች ተሰልፎ ተጫውቷል።

በዘረንቶስ ሰለሞን

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: