በሦስተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በኢሚሬትስ ቼልሲን ያስተናገደው አርሰናል 2 ለ 1 በማሸነፍ ሶስተኛ ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል።
አዲስ ፈራሚው ሞርጋን ሮጀርስ ጨዋታው በተጀመረ በ2ኛው ደቂቃ ባሰቆጠራት ግብ ቼልሲን ቀዳሚ ቢያደርግም፣ 25ኛው ደቂቃ ላይ ካይ ሃቨርትዝ የአርሰናልን የአቻነት ግብ አስቆጥሮ የመጀመሪያው አጋማሽ 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ተጠናቅቋል።
ሆኖም በሁለተኛው አጋማሽ 50ኛው ደቂቃ ላይ ማርቲን ኦዲጋርድ ያስቆጠራት ግብ አርሰናልን አሸናፊ አድርጋለች።
ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል በሦስት ተከታታይ ድሉ በ9 ነጥብ ከሲቲ በግብ መጠን ተበልጦ ሁለተኛ ላይ ተቀምጧል። ቼልሲ በአንፃሩ በ6 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
አርሰናል በ4ኛው ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር ቀጣይ ቅዳሜ ወደ ስታዲየም ኦፍ ላይት አቅንቶ ሰንደርላንድን ሲገጥም፣ ቼልሲ በተመሳሳይ ቅዳሜ ቀን በስታምፎርድ ብሪጅ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ አዲስ አዳጊውን ሃል ሲቲን ያስተናግዳል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: