Search

ድሮኖች በቻይና የግብርና ምርታማነትን እየቀየሩ ነው

ማክሰኞ ሐምሌ 07, 2018 108

በቻይና ደቡባዊ ክፍል፣ በጓንግዶንግ ግዛት የዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም እየተስፋፋ ይገኛል። በተለይም ድሮኖች ሩዝን በመዝራት የእርሻ ሥራን እጅግ ፈጣንና ቀልጣፋ እያደረጉት ነው።

በጓንግዙ ከተማ ሁዋንግፑ ወረዳ ሊያንታንግ መንደር የምትገኝ አንዲት ድሮን፣ በ30 ደቂቃ ውስጥ ብቻ 20 ሄክታር የሚሆን የሩዝ እርሻ መዝራት እንደምትችል ተገልጿል።

በተጨማሪም በእርሻው ውስጥ የተገጠሙ የ"ኢንተርኔት ኦፍ ቲንግስ" (IoT) መሣሪያዎች፣ የአፈር ሴንሰሮች፣ የአየር ሁኔታ ጣቢያዎች እና ስማርት ካሜራዎች በየ15 ደቂቃው መረጃን ወደ የእርሻ መረጃ ማዕከል በመላክ የእርሻ አስተዳደርን በዘመናዊ መንገድ እየደገፉ ይገኛል።

የኢክስኤጂ (XAG) የግብርና ሮቦት ኩባንያ ተባባሪ መስራችና ከፍተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት ጎንግ ጂያቺን እንደገለጹት፣ አንድ ድሮን እስከ 33 ሄክታር የእርሻ መሬትን በመቆጣጠር ሙሉ በሙሉ በሰው እጅ ያልተነካ ዘመናዊ የእርሻ ሥራን ማከናወን ያስችላል።

ይህ ቴክኖሎጂ የግብርና ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ፣ የሥራ ቅልጥፍናን በማሻሻል ዘመናዊ የእርሻ አስተዳደርን ለማጠናከር ትልቅ ሚና እየተጫወተ ነው።

በቃልኪዳን ማዕድን

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: