Search

የመደመር መንግሥት የዜጎችን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ዘርፈ ብዙ የልማት ተግባራትን አከናውኗል - ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

ሰኞ ሐምሌ 20, 2018 16

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (/) በክልሉ ምክር ቤት 6 ዙር 5 ዓመት የሥራ ዘመን 10 መደበኛ ጉባዔ ላይ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

በሪፖርታቸው መንግሥት በበደሎች እና ቁርሾዎች ላይ እርቅን በማውረድ ዘላቂ ሰላም እና የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ዐበይት ተግባራትን ማከናወኑን ገልጸዋል።

በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በክልሉ በተከናወኑ የኢኮኖሚና ግብርና ሥራዎች 23.2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የምርት መጠን የተሰበሰበ ሲሆን፣ 61 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ቀርቧል።

በማዕድን ዘርፉም 348 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ መደረጉን እንዲሁም ከፍተኛ መጠን ያለው የድንጋይ ከሰልና የኮንስትራክሽን ማዕድን መመረቱን ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።

በማኅበራዊ ዘርፍትምህርት ለትውልድንቅናቄ በተሰበሰበ 832 ሚሊዮን ብር 45 ሞዴል ቅድመ-አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተገንብተው ለአገልግሎት በቅተዋል።

በተጨማሪም የንጹህ መጠጥ ውኃ ሽፋን 44 በመቶ መድረሱ እና የዲጂታል አቅምን ለማሳደግ 43 ሺህ በላይ ዜጎች "5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ" የሥልጠና ማረጋገጫ ማግኘታቸው በሪፖርቱ ተመላክቷል።

ቀልጣፋ የመንግሥት አገልግሎትን ለማስፋፋትም በልዩ ልዩ የክልሉ ከተሞች ስድስት "መሶብ" ማዕከላት ተመርቀዋል።

ክልሉ በበጀት ዓመቱ 18.2 ቢሊዮን ብር በላይ የውስጥ ገቢ በመሰብሰብ 64 በመቶ የበጀት ፍላጎቱን በራሱ አቅም መሸፈን መቻሉን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ በአሁኑ ወቅት የምክር ቤቱ አባላት ባቀረቡት በዚህ ዝርዝር ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት እያደረጉ እንደሚገኙ ታውቋል።

በሰለሞን በረና

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: