Search

የስልታዊ ቡድን ምክክር ዛሬም ቀጥሎ ውሏል

ሓሙስ ሐምሌ 23, 2018 47

በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው 250 አባላት ባሉት 16 ስልታዊ ቡድኖች የተደራጁ ተመካካሪዎች ምክክር ዛሬ ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጥሎ ውሏል፡፡

በ250 አባላት የተደራጁ 16 ስልታዊ ቡድኖች ከጥቃቅንና ንዑስ ቡድኖች በተገኙና በተጠናቀሩ የአጀንዳ ምክረሃሳቦች ላይ ከትላንት ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምረው ተመካክረዋል፡፡

ትላንት ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በነበረው የምክክር ውሎ ከእያንዳንዱ ስልታዊ ቡድን በተመረጡ 25 የአጀንዳ ምክረ-ሃሳብ አጠናካሪዎች አማካኝነነት የተጠናቀሩ ምክረሃሳቦችን ያዳመጠው 16ቱ ባለ 250 አባላት ስልታዊ ቡድን አባላት፣ በጥቃቅንና በንዑስ ቡድኖች ተነስተው በቀረበው ቃለ ጉባኤ ላይ ያልተካተቱ፣ በአግባቡ ያልተብራሩ ያላቸውን ሃሳቦች ማቅረቡ አይዘነጋም፡፡

ስልታዊ ቡድኖቹ በዛሬው ውሏቸው የተሰጡ አስተያየቶች ተካተውበት በድጋሚ የተደራጀውን ቃለ ጉባኤ የጋራ በማድረግ በቀጣይ ለሚደረገው እና 500 ተመካካሪዎችን ለያዙ 8 ቡድኖች ምክክር ዝግጅት ሲያደርጉ ውለዋል፡፡

በነገው ዕለት በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ላይ እገዛ የሚያደርጉ የክልል (ከተማ መስተዳደር) እና የፌዴራል ተወካዮች ምርጫ የሚደረግ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: