Search

የባሕር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ከታክስ በፊት 28.2 ቢሊዮን ብር ትርፍ አገኘ

ሓሙስ ሐምሌ 23, 2018 62

የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ በ2018 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 28.2 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል።

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አብዱልበር ሸምሱ በሰጡት መግለጫ፣ ተቋሙ በተጠናቀቀው 7.04 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ጭነት ማጓጓዝ መቻሉን አመልክተዋል።

በበጀት ዓመቱ 144.9 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት መታቀዱን አንስተው፣ 157.2 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉንና ይህም የዕቅዱን 108.5 በመቶ መሆኑን ጠቁመዋል።

አፈጻጸሙም ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ27 በመቶ ብልጫ እንዳለው ዋና ሥራ አስፈጻሚው አመልክተዋል።

ተቋሙ ከ20 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነዳጅ ማጓጓዝ የጀመረ ሲሆን፣ ይህም አጠቃላይ ካጓጓዘው ጭነት የ1.7 በመቶ ድርሻ እንደሚይዝ አመልክተዋል።

በዓመቱ 2 ሚሊዮን ቶን የአፈር ማዳበሪያ መጓጓዙንና ከዚህ ውስጥ 74 በመቶው በተሽከርካሪ እንዲሁም 26 በመቶው በባቡር ትራንስፖርት ለተጠቃሚዎች መድረሱን ጠቅሰዋል።

ተቋሙ በ2030 የኢትዮጵያን የኮንቴይነር አቅርቦት 100 ሺህ ለማድረስ ያለመ ሲሆን፣ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለኤክስፖርተሮች 34 ሺህ ኮንቴይነሮች ማቅረብ መቻሉ በዚሁ ወቅት ተገልጿል።

በኤዶም አማረ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: