የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታችን በእመርታ የሚያድግበት ዘመን ላይ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ፡፡
የብሔራዊ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ስብሰባውን አካሂዷል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልእክት፤ ምክር ቤቱ በዓመቱ ውስጥ እንዲፈፀሙ ያስቀመጣቸውን ተግባራት አፈፃፀም በጥልቀት በማየት አቅጣጫ አስቀምጧል ብለዋል።
የብሔራዊ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤቱ አጠቃላይ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የስራ ክንውን፣ የዲጂታል መታወቂያ የምዝገባ ሂደት እንዲሁም ‘የ5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ኮደርስ’ ኢኒሼቲቭ ትግበራ አፈጻጸምን ገምግሞ በቀጣይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከስምምነት ላይ መደረሱንም ጠቅሰዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በሀገራችን በመከናወን ላይ የሚገኙ አዳዲስ የዲጂታል ስራዎች ከዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ ጋር ያላቸውን ተጣጣሚነትን በውይይታችን ተመልክተናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታችን በእመርታ የሚያድግበት ዘመን ላይ እንደመሆኑ፤ ምክር ቤቱም ለዚሁ ዕድገት ተገቢውን ሚና ለመወጣት የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: