Search

የዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን ትኩረት የሳበው የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ

ማክሰኞ ሐምሌ 28, 2018 52

ኢትዮጵያ ሐምሌ 27 ቀን 2018 . ባካሄደችው ታሪካዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር፣ በአንድ ጀምበር 805 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ያስመዘገበችው ስኬት የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃንን ቀልብ ስቧል።

የውጪ ሚዲያዎች በዘገባዎቻቸው፤ ወደ 26 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች በነቂስ በመውጣት ያሳዩትን ታሪካዊ ተሳትፎ እና የባለቤትነት ስሜት በከፍተኛ አድናቆት አስነብበዋል።

በተለይም ዓለም በከባድ የአየር ንብረት ለውጥ እና የበረሃማነት ስጋት ውስጥ ባለችበት በዚህ ወቅት፣ ኢትዮጵያ በራሷ አቅም የደን ሽፋኗን ለማሳደግ እና የውኃ ምንጮቿን ለመታደግ እያደረገችው ያለው ተቋማዊና ሕዝባዊ ጥረት በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደር የሌለው መሆኑን ዘገባዎቹ አጉልተዋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመሆን ያከናወኑት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የዘመቻውን ዓለም አቀፋዊ አድማስ ማስፋቱን ጠቁመዋል።

ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ይህን ግዙፍ ሀገራዊ ንቅናቄ በስፋት ማስተጋባታቸው፣ ኢትዮጵያ ለምድር ጤናማነት እና ለዘላቂ ልማት ያላት ቁርጠኝነት ለአፍሪካም ሆነ ለተቀረው ዓለም ትልቅ ተሞክሮ መሆኑን ያረጋግጣል።

በሃና ምንዳሁን

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: