ከ100 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ የፀሐይ ግርዶሽ በዋናው የስፔን ክፍል ሊታይ መሆኑ የሥነ ፈለክ ባለሙያዎችንና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተመልካቾችን ቀልብ አግኝቷል።
ይህ ታላቅ የተፈጥሮ እና የሰማይ ላይ ክስተት ነሃሴ 6 ቀን 2018 የሚከሰት መሆኑ ተገልጿል። በዚህ ዕለት ጨረቃ በፀሐይና በምድር መካከል በቀጥታ ስትገባ የፀሐይን ብርሃን ሙሉ በሙሉ በመሸፈን በቀን መካከለኛ ሰዓት ውስጥ እንደ ሌሊት ያለ ድንገተኛ ጨለማ እንዲፈጠር ታደርጋለች።
ይህ አስደናቂ ግርዶሽ በአይቤሪያ ባሕረ ገብ መሬት አካባቢ በተለይም በስፔንና በፖርቱጋል ክፍሎች በግልጽ የሚታይ ሲሆን፣ በግሪንላንድና በአይስላንድ የተወሰኑ ስፍራዎችም ለመመልከት ያስችላል።
የዚህ ሙሉ የፀሐይ ግርዶሽ የቆይታ ጊዜም እስከ 2 ደቂቃ ከ18 ሰከንድ ድረስ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ባለሙያዎች ይህን ክስተት ከቀጣዩ ዓመት ከሚጠበቀው ይበልጥ ረጅም የፀሐይ ግርዶሽ የሚያስታውቅ ቅድመ ማሳያ መሆኑን እየተናገሩ ይገኛሉ።
በተጨማሪም በዚሁ ወቅት ዝናብ እና የስድስት ፕላኔቶች ሰልፍ መኖሩ የሰማይ ተመልካቾችን የበለጠ እንደሚስብ ተጠቁሟል። የሥነ ፈለክ ባለሙያዎች የፀሐይ ግርዶሽን በቀጥታ ለመመልከት ልዩ የዓይን መከላከያ መነጽሮችን መጠቀም እንደሚገባ በጥብቅ አሳስበዋል።
ይህ ልዩ የሰማይ ክስተት በአውሮፓ ከብዙ አሥርት ዓመታት በኋላ የሚታይ አስደናቂ ተፈጥሯዊ ሁነት በመሆኑ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቱሪስቶችና የዘርፉ ተመራማሪዎች በጉጉት እንደሚከታተሉት ይጠበቃል።
በቃልኪዳን ማዕድን
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: