የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
ምክር ቤቱ የክልሉን የ2019 አጠቃላይ ረቂቅ በጀት ላይ ውይይት በማድረግ በጀቱ 67 ቢሊየን ብር እንዲሆን በአብላጫ ድምፅ አጽድቋል።
ከጠቅላላው በጀት ውስጥ 47 በመቶው በመንግሥት ግምጃ ቤት የሚሸፈን ሲሆን፣ 53 በመቶው ደግሞ ከክልሉ የውስጥ ገቢ እንደሚሸፈን ተገልጿል።
የ2019 በጀት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ30.3 ቢሊየን ብር ጭማሪ እንዳለው የተገለጸ ሲሆን፣ በምክር ቤቱ በ2018 በጀት ዓመት ሪፖርት እና የ2019 ጠቋሚ እቅድ ላይ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
በቶማስ ኃይሉ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: