Search

አስተማማኝና ዘላቂ ጤና በአቋራጭ መንገድ አይገኝም፦ ዶክተር መቅደስ ዳባ

ዓርብ ነሐሴ 01, 2018 121

ጤና ሚኒስቴር "የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ጤናዎን ይጠብቁ"  በሚል መሪ ሐሳብ ማኅበረሰቡን ያሳተፈ ሳምንታዊና ወርሃዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እየተገበረ ይገኛል።

ሚኒስቴሩ ይህንን ወርሃዊ የስፖርት አንቅስቃሴ በባሕር ዳር ከተማ በዛሬው ዕለት ያካሄደ ሲሆን፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በዚሁ ወቅት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ሥርጭት አሳሳቢ መሆኑን አንስተዋል።

ስፖርት ጤናን መጠበቂያ፣ መከላከያና አክሞ ማዳኛ መንገድ በመሆኑ በትኩረት እየተሠራበት መሆኑን ገልጸዋል።

የጋራ ስፖርት እንደ ጤና ሚኒስቴር በየወሩ በተለያዩ አካባቢዎች እየተተገበረ መሆኑን ጠቁመው፣ ይህንንም ወደባህል በመቀየር የሁልጊዜ ተግባር ወደ ማድረግ መሻገሩን አስረድተዋል። 

ማኅበረሰባችን የሰዎችን አካላዊ ለውጥና ማንነት የመቀበል እሳቤ በማኅበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ስር መውደቁን ያነሱት ሚኒስትሯ፣ አካላዊ ውፍረት ለመቀነስና ጤናን ለመጠበቅ የሚደረጉ አቋራጭ መንገዶች የሚያስከትለው ጉዳት የከፋ ስለመሆኑ አስገንዝበዋል።

የጋራ እና የግል አካላዊ እንቅስቃሴን የዕለት ተዕለት ልምድ ማድረግ እና በባለሙያና በጤና ተቋም የሚደረጉ እገዛዎችን መከተል ትክክለኛ መፍትሄ የሚያመጣ ስለመሆኑም አስረድተዋል።

ጤና ሚኒስቴር የተጠናቀቀውን በጀት ዓመት አፈፃፀም ከክልል የጤና ቢሮ ኃላፊዎችና የዘርፉ አጋር አካላት ጋር በባሕር ዳር ከተማ እየገመገመ ይገኛል።

በራሔል ፍሬው

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: