Search

"ኦሮሞ ኢትዮጵያ ነው፤ በገዛ ሀገሩ ውስጥ ድንበር የሌለው የሀገር ባለቤት"፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ቅዳሜ ነሐሴ 02, 2018 317

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) የኦሮሞ ሕዝብ ከኢትዮጵያ ሀገር ግንባታ ጋር ያለውን ጥብቅ ቁርኝት እንዲሁም በፖለቲካው ዘርፍ ሲሰነዘሩ የነበሩ የተሳሳቱ ትርክቶችን በሚከተለው መልኩ አብራርተዋል፡-

የኦሮሞ ሕዝብ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ አድርጎ በመፍጠር እና በመገንባት ረገድ መሠረታዊ እና ግንባር ቀደም ሚና እንዳለው ገልጸዋል። በመሆኑም ሕዝቡ በገዛ ሀገሩ ውስጥ ድንበር የሌለው የሀገር ባለቤት መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

የመገንጠል ጥያቄን ውድቅ ባደረጉበት ንግግራቸው፣አባቶቹ ላቡን፣ ደሙን እና አጥንቱን ገብሮ የገነባትን ሀገር የኦሮሞ ሕዝብ ሊያፈርስም ሆነልገንጠልየሚል ጥያቄ ሊያነሳ አይችልም፤ ይህን ማድረግም ታሪካዊ ስህተት ነውብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን መሰሉን ጥያቄ "የደካማ እና የጭንቀት ጥያቄ" ሲሉ ገልጸውታል።

"ጠባብ" የሚለውን ፍረጃ ሲቃወሙ፣ የኦሮሞ ሕዝብ በማንኛውም አጋጣሚ ሌላውን አቅፎ የራሱ አድርጎ የሚያሳድግ (ሰፊ የማካተት ባህል ያለው) ትልቅ ሕዝብ እንደሆነ አስምረውበታል።

ይህ ሆኖ ሳለ በፖለቲካው ሥርዓትጠባብየሚል ስያሜ ተሰጥቶት ሕዝቡን ለማሸማቀቅ እና ስሙን ለማጥፋት የተደረገው ሙከራ ፍጹም ስህተት እና አግባብነት የሌለው መሆኑን አስረድተዋል። የዚህን ሕዝብ አስተዋጽኦ መቀነስ የሀገርን ሰላም እንደማያመጣም ጠቁመዋል።

የኦሮሞ ሕዝብ የሺህ ዓመታት የሀገር ግንባታ ታሪክን በተመለከተ፦ የኦሮሞ ሕዝብ ለኢትዮጵያ ሀገር ግንባታ ያበረከተው አስተዋጽኦ 400 ወይም 500 ዓመታት ታሪክ ብቻ ሳይሆን፣ 800 እስከ 1,000 ዓመታት ወደኋላ የሚመለስ ጥልቅ ታሪክ መሆኑን ነው የገለጹት። አክሱምን፣ ላሊበላን እና ምጽዋን ጨምሮ በየትኛውም የሀገራችን ታሪካዊ ስፍራዎች የኦሮሞ ሕዝብ እጅ እና አሻራ ያረፈበት መሆኑን አብራርተዋል።

ኦሮሞ ኢትዮጵያን ገንብቷል፤ ኢትዮጵያም የኦሮሞ ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ በመሆኑም ሕዝቡ አባቶቹ የገነቡትን ሀገር ወደማፍረስ በፍጹም እንደማይሄድ እምነታቸውን ገልጸዋል።

በዮናስ በድሉ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: