Search

"ከብክለት ነጻ የሆነች ኢትዮጵያን ለትውልድ!" የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በእንጦጦ አረንጓዴ አሻራውን አኖረ

ቅዳሜ ነሐሴ 02, 2018 115

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አመራሮችና ሰራተኞች ከብክለት ነጻ የሆነችና የተፈጥሮ ስነምህዳሯ የተጠበቀች ኢትዮጵያን ለመጭው ትውልድ የማስረከብ ራዕያቸውን ሰንቀው በእንጦጦ አካባቢ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናውነዋል።

በዚሁ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ላይ የተሳተፉት የባንኩ ኤክስኪዩቲቭ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ እንዳስታወቁት፣ የተፈጥሮ ስነምህዳሯ የተጠበቀችና አረንጓዴ አገርን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስረከብ ችግኝ መትከልና መንከባከብ ወሳኝ ሚና አለው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዘንድሮው መርሃ ግብር 250 ሺህ በላይ ችግኞችን ለመትከል ማቀዱን የገለጹት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፣ አረንጓዴ አሻራን ማኖር በባንኩ ሰራተኞች ዘንድ መልካም ባህልና የዘወትር ልምድ እየሆነ መምጣቱን አብራርተዋል።

በዕለቱ አረንጓዴ አሻራቸውን ያኖሩት የባንኩ ሰራተኞችም በተፈጥሮ ጥበቃው ላይ የድርሻቸውን በማበርከታቸው የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቀጣይም ከችግኝ ተከላው መርሃ ግብር ባለፈ በሌሎች ሀገራዊ የልማት ስራዎች ላይ የሚያደርገውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

በመሀሪ አለሙ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: