Search

በኢትዮጵያ የመጣው ለውጥ በምሥራቅ አፍሪካም ሆነ በዓለም ደረጃ የሚደነቅ ነው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ቅዳሜ ነሐሴ 02, 2018 166

ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ባስመዘገበችው አጠቃላይ የልማት እና የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የኦሮሞ ሕዝብ ሀገር የመገንባት፣ የመምራት እና የማልማት ታላቅ አቅም በተግባር መረጋገጡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኦቢኤን ጋር በተነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፣ በሀገራችን የመጣው አጠቃላይ ለውጥ በምሥራቅ አፍሪካም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ዕውቅናና አድናቆት ያተረፈ ነው።

ይህ ውጤት ሊገኝ የቻለው ሕዝባችን በሥርዓት ማሰብ እና መሥራት በመቻሉ፣ የአዕምሮአዊ አስተሳሰብ ለውጥ በመምጣቱ እና በመንግሥት እና በሕዝብ መካከል ጠንካራ ቅንጅት በመፈጠሩ እንደሆነ አብራርተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኦሮሚያ ክልል የተመዘገበውን የበጀት ዕድገት ሲያብራሩ፣ 2010 . የክልሉ በጀት 50 ቢሊዮን ብር ገደማ የነበረ ሲሆን፣ በዘንድሮው በጀት ዓመት የጸደቀው የበጀት መጠን ግን ወደ 274 ቢሊዮን ብር ማደጉን ጠቁመዋል።

የበጀቱ በከፍተኛ ሁኔታ ማደግ የልማት ሥራዎች እንዲስፋፉ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች እንዲሻሻሉ፣ የከተሞች ዕድገት እና የመሠረተ ልማት ዝርጋታዎች እንዲፋጠኑ ማስቻሉን አስረድተዋል።

ከስድስት እና ሰባት ዓመታት በፊት የነበረውን የከተሞች ሁኔታ ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ቀደም ሲል ከተሞች ያለ ምንም ፕላን እና ቅደም ተከተል በዘፈቀደ መልክ ግንባታ የሚካሄድባቸው፣ መንገዶቻቸው ለእግረኛ እንኳ የማይመቹ እንደነበሩ ገልጸዋል።

ዛሬ ግን እንደ ቢሾፍቱ፣ አዳማ፣ ጅማ፣ ሮቤ፣ ማያ፣ ነቀምቴ እና ሻሸመኔ ያሉ ከተሞቻችን የሥራ ዕድል፣ የንግድ እንቅስቃሴ እና የሀብት ማፍሪያ ማዕከላት በመሆን የደረጃ እና የገጽታ ለውጥ አድርገዋልነው ያሉት።

የከተሞች መስፋፋት ተገቢውን የአገልግሎት አሰጣጥ፣ ትምህርት ቤቶችን፣ ጤና ጣቢያዎችን እና መሠረተ ልማቶችን በማሟላት የሕዝቡን ጥያቄዎች እየመለሰ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

ይህ የታሪክ ለውጥ የኦሮሞን ሕዝብ ጥያቄዎች ሙሉ በሙሉ መመለስ ባይችልም፣ ትልቅ ተስፋ እና አቅጣጫ ማሳየት መቻሉንም ገልጸዋል።

ታላቁ ድል የተገኘው በተደረጉ ትግሎች፣ በተከፈሉ መሥዋዕትነቶች እና በጠንካራ ሥራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

በታሪክ ሒደት ውስጥ የኦሮሞ ማንነት እና አስተዋጽኦ ዝቅ ተደርጎ ይታይ የነበረበትን ሁኔታ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ኦሮሞ ሀገር ማልማት እና ማስተዳደር አይችልምየሚለውን የተሳሳተ አስተሳሰብ በተግባር ማረም መቻሉን አብራርተዋል።

ዛሬ ኢትዮጵያን የማልማት፣ ሀገር የመምራት፣ የለውጥ አየር የማምጣት እና ዓለም የሚደነቅበትን ሥራ የመሥራት አቅም እንዳለን በተግባር አሳይተናል ብለዋል።

በኢንዱስትሪ፣ በቱሪዝም፣ በግብርና እና በከተሞች ልማት የተመዘገበው ውጤት ከወላጆች እና የአባቶች ውርስ፣ ከገዳ ሥርዓት ዕሴቶች እንዲሁም ከአዲስ ዕውቀት እና ጥበብ ጋር በመቀናጀት የመጣ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በኢኮኖሚው ዘርፍ በግብርና ብቻ ሳይሆን በሁሉም ዘርፎች ሰፊ የልማት ጅምሮች መኖራቸውን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የምርት መጠን 163 ሚሊዮን ኩንታል ወደ 550 ሚሊዮን ኩንታል ማደጉን እንደ ትልቅ እና አበረታች ውጤት ጠቅሰውታል።

በመሐመድ ፊጣሞ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: