Search

የባሕር በር ጥያቄ፦ የሰላምና የጋራ እድገት ጥሪ

ቅዳሜ ነሐሴ 02, 2018 141

የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ከማንኛውም ቀጣናዊ የጥቅም ግጭት ወይም የኃይል ፍላጎት የፀዳ፤ ይልቁንም የጎረቤቶቿን ሉዓላዊነት በሚያከብር፣ በሰላማዊ ዲፕሎማሲ እና በጋራ የመልማት መርህ ላይ የተመሰረተ ነው።

የባሕር በር የዓለም አቀፍ የኢኮኖሚያዊ ትስስር ደምስር በሆነበት በዚህ ዘመን፣ የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ አማራጭ ሣይሆን የህልውና ጉዳይ ነዉ።

ይህ ጥያቄ የአንድን ወገን ጥቅም የሚጎዳ ሳይሆን፣ ቀጣናውን ሙሉ በሙሉ ወደተሻለ የኢኮኖሚ ምዕራፍ የሚያሸጋግር የሰላም እና የእድገት መሠረት ነው።

የጎረቤት ሀገራትን ሕጋዊ አካልነት እና ግዛት አንድነትን ሙሉ በሙሉ በማክበር፣ ፍታዊ በሆነ የንግግር እና የድርድር መድረክ የጋራ እድገትን ማረጋገጥ ይቻላል።

በጋራ ኢንቨስትመንት፣ የወደብ አልሚነት ተሳትፎ፣ የጋራ የንግድ ቀጠናዎችን በመፍጠር እንዲሁም የኃይል እና የመሠረተ-ልማት አቅርቦቶችን ለጎረቤት ሀገራት በማቅረብ የሚደረግ ስምምነት የሁሉንም ወገኖች ጥቅም በእኩልነት ያረጋግጣል። ይህም የወደብ ባለቤት የሆኑ ሀገራትን ኢኮኖሚ ከማሳደጉም በላይ ቀጣናዊ ወንድማማችነትን ያጠናክራል።

በመሆኑም፣ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ዓለም አቀፍ ህጎችን፣ የሰላማዊ ጉርብትና መርሆዎችን እና ፍትሐዊ አሰራርን የተከተለ ጥያቄ ነው።

ይህ ጥያቄ በሰላማዊ የዲፕሎማሲ መድረኮች ሲመለስ፣ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እምቅ አቅም ከመክፈቱ ባሻገር ለአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላም፣ መረጋጋት እና የጋራ ብልፅግና አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የሚከፍት ይሆናል።

በሔዋን ጌታቸው

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: