Search

የአፋር ክልል ምክር ቤት 10ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ

ቅዳሜ ነሐሴ 02, 2018 122

የአፋር ክልል ምክር ቤት 6 ዙር፣ 5 ዓመት የስራ ዘመን፣ 10 መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል።

ምክር ቤቱ ለሚቀጥሉት ሶስት ቀናት በሚያካሂደው በዚህ ጉባዔ፤ በክልሉ አስፈጻሚ አካላት፣ በጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የቀረቡትን 2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቶች ላይ ሰፊ ውይይት የሚያደርግ ይሆናል።

በጉባዔው መክፈቻ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ 2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል የተከናወኑ ተግባራትን፣ ከአጎራባች ክልሎች ጋር ህዝባዊ ውይይቶችን በማድረግ ረገድ የተገኘውን ሰላምና መልካም ግንኙነት እንዲሁም በአጠቃላይ በክልሉ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና በሰላም ዙሪያ የተከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎችን አብራርተዋል።

በሌላ በኩል፣ የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባዔ ወይዘሮ አሲያ ከማል ጉባዔውን ሲያስጀምሩ ባደረጉት ንግግር፣ ምክር ቤቱ በህዝብ የተሰጠውን አደራ በመወጣት የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ተግባራትን በየደረጃው ማከናወን መቻሉን ገልጸዋል።

 በአሊ አህመድ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: