የላቁ የዲጂታል መድረኮችን መገንባት እና ሙሉ ለሙሉ ወደ ዲጂታል አሰራር መሸጋገር ግድ መሆኑን ገልጸው ለተግባራዊነቱና የዘመነ አፈጻጸም የሰለጠነ የሰው ኃይል እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።
የሰዎችን አቅም ማጎልበት፣ አሳታፊ የዲጂታል ምህዳር መፍጠር፣ ተዳራሽነትን ማስፋፋት እና ሀገሪቱን የዲጂታል ማዕከል ማድረግ ላይ ትኩረት ባደረገው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ግቦች ስር እያንዳንዱ በቴክኖሎጂ ዘርፍ የሚመዘገብ ስኬት ሙሉ በሙሉ በሰው ሃይል አቅም ላይ የተመሰረተ እንደሆነ አብራርተዋል።
ይህን አቅም ወደ ተግባር ለመቀየር ደግሞ ወጣቶች በየተሰማሩበት ዘርፍ ክህሎታቸውን በንቃት ማሳደግ እና ለላቀ ውጤታማነት መጠንከር እንዳለባቸው ገልጸዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: